መኢአድ በጉጂ ዞን በምርጫ ለመወዳደር ጽህፈት ቤት ከፍቶ እየተንቀሳቀሰ ነው
ነገሌ, መጋቢት 3 ቀን 2002 (ነገሌ) - የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት / መኢአድ/ በጉጂ ዞን በመጪው ግንቦት ወር በሚካሄደው ብሄራዊ ምርጫ ለመወዳደር በዞን ደረጃ

ጽህፈት ቤት ከፍቶ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን አስታወቀ፡፡

በድርጅቱ የጉጂ ዞን ጽህፈት ቤት ዋና ጸሐፊ መቶ አለቃ ንጉሴ ሰለሞን ለኢዜአ.እንደገለጹት ድርጅቱ በዞኑ ነገሌ ቦረና ከተማ ካለፈው ታህሳስ ወር ጀምሮ ጽህፈት ቤት ከፍቶ በምርጫው ለመወዳደር እየሰራ ነው፡፡

በዞኑ በኡራጋ፣ በቦሬ፣ ቀርጫ ወረዳዎችና በነገሌ ቦረና ከተማ ድርጅቱን ወክለው የሚወዳደሩ ለህዝብ ተወካዬች ምክር ቤት አምስት

ለክልል ምክር ቤት ደግሞ አስር እጩዎች ማስመዝገቡን አስታውቀዋል፡፡

እንደ መቶ አለቃ ንጉሴ ማብራሪያ የዕጩዎቹ ስም ዝርዝር በግልጽ በሚታይበት ቦታ ተለጥፎ ለህዝብ ይፋ ሆኗል፡፡

በተጨማሪም ድርጅቱ በሂደት የሚያጋጥሙ ችግሮችን በውይይት በመፍታት ምርጫው ሰላማዊ፣ ፍትሃዊ፣ዴሞክራሲያዊና በሁሉም

ዘንድ ተዓማኒ እንዲሆን ከኦህዴድ/ኢህአዴግ ጋር የጋራ ምክር ቤት አቋቁሞ አብሮ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ሪፖ ኤዲ፣ከ9፡00-9፡40፣አጥ

---END---

Headlines
መኢአድ በጉጂ ዞን በምርጫ ለመወዳደር ጽህፈት ቤት ከፍቶ እየተንቀሳቀሰ ነው
በጎንደር ከተማ የዕጩዎች ስም ዝርዝር ለህዝብ ይፋ ሆነ
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን የ33 ዋና ዋና መንገዶች ዲዛይኖችን በማጠናቀቅ ላይ እንደሚገኝ አስታወቀ
የእንግሊዝ ሲቪል ሰርቪስ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ላለው የሲቪል ሰርቪስ ማሻሻያ ድጋፍ እንደሚሰጥ ገለጸ
አዋሬ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የተገነባው አደባባይ በጀርመኗ ላይፕዚች ከተማ ስም ተሰየመ
በአርብቶ አደሩ አኗኗ ሁኔታ፣ ባሉበት ችግሮችና በሌሎችም ተዘማጅ ጉዳዮች ላይ መሰረታዊ መረጃ ለማቅረብ የተካሄደው ጥናት ይፋ ሆነ
የዲያስፖራ ዳይሬክት ኢንቨስትመንት የብድር አገልግሎት ባለፈው ዓመት 45 ሚሊዮን ዶላር ማበደሩን አስታወቀ
በሀረሪ ክልል በየዘርፉ አበረታች ተግባራት ተከናውነዋል
(c) The Ethiopian News Agency