አዲስ አበባ, መጋቢት 3 ቀን 2002 (አዲስ አበባ) - ሴቶችን በህገ መንግስታዊ መብቶቻቸው ተጠቃሚ ለማድረግ ሰፋ ያለ እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ አስታወቁ፡፡
ምክር ቤቱ በኢትዮጵያ ለ34ኛ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ ደግሞ ለ99ነኛ ጊዜ የተከበረውን ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን /ማርች 8/ ምክንያት በማድረግ ባዘጋጀው ፕሮግራም ላይ ምክትል አፈ ጉባኤ ሽታዬ ምናለ እንደገለጹት ሴቶችን በልማቱና በዴሞክራሲው በይበልጥ ተጠቃሚ ለማደረግ የሚያስችሉ እንቅስቃሴዎች ተደርገዋል፡፡
መንግስት በህዝብ ተሳትፎ የሴቶችን እኩልነት የሚያረጋግጡ ህጐችን ከማውጣት ጀምሮ ተሳታፊና ተጠቃሚነታቸውን የሚያረጋግጡ ዝርዝር ህጎች፣ፖሊሲዎችና ፓኬጆችን ቀርጾአል፡፡
በአሁኑ ጊዜም የሴቶች ፖለቲካዊ፣ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተሳትፎ እየጎለበተና ተጠቃሚነታቸውም እየተረጋገጠ ይገኛል ብለዋል፡፡
የሴቶችን መብትና ነጻነት ማክበር የአገር ልማትና የዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታን ማፋጠን ነው ያሉት ምክትል አፈ ጉባኤዋ ሴቶችን በሁለንተነዊ እንቅስቃሴ ማሳተፍ ለሴቶች ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ ለአገር እድገት ወሳኝና ቁልፍ ሚና አለው ብለዋል፡፡
በተለይም በስራ ላይ የሚደረግ አድሎአዊ አሰራር እንዲቆምና በልዩ ልዩ መሰኮች እኩልነታቸው እንዲረጋገጥ በርካታ ስራዎች ሲሰሩ ቆይተዋል ወደፊትም ይሰራሉ ብለዋል፡፡
የተሳኩ ተሞክሮዎች በተቀናጀ የሴቶች ንቅናቄ ይስፋፋሉ በሚል መርህ የተከበረው የሴቶች ቀን ዋና ዓላማም የሴቶችን ሁለንታናዊ ተሳትፎ በማጎልበት የሀገሪቱን እድገትና ልማት ቀጣይነት ለማረጋገጥ ሁሉም የበኩሉንና ድረሻ እንዲወጣ መልዕክት ለማሰተላለፈ ነው ብለዋል፡፡
በበዓሉ ላይ ሴቶች በህገ መንግስታዊ መብቶቻቸው ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ እያደረጉት ያለውን እንቅስቃሴ የሚያሳይ ድራማ፣ መዘሙርና ልዩ ልዩ ዝግጅቶች ቀርበዋል፡፡
ስ.3.00 የ.5.55 ሪ.6.42 ያ.9.10 ኤ10፡46
---END---