ፕሬዚዳንት ግርማ የሥራ ጊዜያቸውን ያጠናቀቁትን በኢትዮጵያ የማላዊ አምባሳደርን አሰናበቱ
አዲስ አበባ, መጋቢት 3 ቀን 2002 (አዲስ አበባ) - ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ የሥራ ጊዜያቸውን ያጠናቀቁትን በኢትዮጵያ የማላዊ አምባሳደርን አሰናበቱ።

ተሰናባቹ አምባሳደር በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን የልማትና የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ በቅርብ ለማየት መብቃታቸውንና ለዚህም ከፍተኛ አድናቆት እንዳላቸው ገልጸዋል።

ፕሬዘዳንት ግርማ ላለፉት አራት ዓመታት በኢትዮጵያ ያገለገሉትን የማላዊ አምባሳደር ጀምስ ዶናልድ ካሊላንጎን ሲያሰናበቱ እንደተናገሩት በሁለቱ አገሮች መካከል ያለውን ግንኙነት በተጠናከረ መልኩ ይቀጥላል።

አምባሳደር ካሊላንጎ ሁለቱን አገሮች ለማቀራረብ ላደረጉት ጥረት አመስግነው፣ በቀጣይ ተሹመው የሚመጡት አምባሳደርም ለአገሮቹ ወዳጅነትና ትብበር እንደሚሰሩ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።

ሚስተር ካሊላንጎ በበኩላቸው በሁለቱ አገሮች መካከል ያለውን ለማሳደግ አጠቃላይ ስምምነት መደረጉን አስረድተው፣በቀጣይ የሚመጡት አምባሳደርም ተጨባጭ በሆኑና ሁለቱ አገሮች ሊተባበሩባቸው በሚችሉ የልማትና የኢኮኖሚ መስኮች ትኩረት ሰጥተው እንደሚሰሩ እምነት አለኝ ብለዋል።

አምባሳደሩ ኢትዮጵያ ውሰጥ ላለፉት አራት ዓመታት በቆዩባቸው ጊዜያት የአገሪቱን ልማትና ዕድገት በቅርብ ሆነው ለመመልከት መቻላቸውን

በሥራቸውም አስፈላጊው ትብብር እንዳልተለያቸው ተናግረዋል ሲል የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዘግቧል።

---END---

Headlines
ፓርቲዎች ሦስተኛ ዙር የምርጫ ክርክራቸውን አካሄዱ
ፕሬዚዳንት ግርማ የሥራ ጊዜያቸውን ያጠናቀቁትን በኢትዮጵያ የማላዊ አምባሳደርን አሰናበቱ
(c) The Ethiopian News Agency