ፓርቲዎች ሦስተኛ ዙር የምርጫ ክርክራቸውን አካሄዱ
አዲስ አበባ, መጋቢት 3 ቀን 2002 (አዲስ አበባ) - በመጪው ግንቦት ወር በሚካሄደው ምርጫ የሚሳተፉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ዛሬ ሦስተኛ ክርክራቸውን ዙር አካሄዱ።

በፓርቲዎች ክርክሩን ያካሄዱት ''መልካም አስተዳደር ፣ ሰብዓዊ መብትና የሕግ የበላይነት'' በሚል ርዕስ ላይ ነው፡፡

በክርክሩ ላይ የተሳተፉት የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር(ኢህአዴግ)፣የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ(መድረክ)፣የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲ ፓርቲ(ኢዴፓ)፣የመላው ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ(መኢዴፓ)፣ቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ(ቅንጅት)ናቸው።

ክርክሩ ዛሬ ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ዜና በኋላ በኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን እንደሚተላለፍም የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዘግቧል።

---END---

Headlines
ፓርቲዎች ሦስተኛ ዙር የምርጫ ክርክራቸውን አካሄዱ
ፕሬዚዳንት ግርማ የሥራ ጊዜያቸውን ያጠናቀቁትን በኢትዮጵያ የማላዊ አምባሳደርን አሰናበቱ
(c) The Ethiopian News Agency