በጉራጌ ዞን ፓርቲዎች 94 እጩዎች አስመዘገቡ
ወልቂጤ, የካቲት 2 ቀን 2002 (ወልቂጤ) - በጉራጌ ዞን በመጪው ግንቦት ወር በሚካሄደው ምርጫ የሚሳተፉ አምስት የፖለቲካ ፖርቲዎች 94 እጩዎች ማስመዝገባቸውን የዞኑ

ምርጫ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

የጽህፈት ቤቱ አስተባባሪ አቶ ፈቃደ መንጀታ ትናንት ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለፁት የም ልዩ ወረዳን ጨምሮ በ13ቱ የምርጫ ክልሎች እጩዎቻቸውን ያስመዘገቡት ደኢህዴን፣ቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ፣ የመላ ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ፣የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያው አንድነት መድረክና ወለንኛ ቋንቋ ተናጋሪ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ናቸው፡፡

ፓርቲዎቹ ካስመዘገቧቸው እጩዎች መካከል 31ዱ ለተወካዮች 63ቱ ደግሞ ለክልል ምክር ቤቶች እንደሚወዳደሩ ተናግረዋል፡፡

በሌላ በኩል በዞኑና የም ልዩ ወረዳን ጨምሮ በተቋቋሙ 836 የምርጫ ክልሎች ይመዘገባል ተብሎ ከሚጠበቀው 560 ሺህ የሚጠጋ

መራጭ ህዝብ ውስጥ 90 ከመቶ የሚሆነው ተመዝግቦ ለመራጭነት የሚያበቃውን ካርድ መውሰዱን ተናግረዋል፡፡

በመራጭነት ከተመዝገቡት መካከልም 247 ሺህ 168 ያህሉ ሴቶች መሆናቸውንም አስረድተዋል፡፡

---END---

Headlines
በምስራቅ ጎጃም 87 በመቶ የሚሆነዉ መራጭ ተመዝግቧል
በጉራጌ ዞን ፓርቲዎች 94 እጩዎች አስመዘገቡ
የሰላሌ የወተት አምራቾች የህብረት ሥራ ዩኒየን አባላት ከፍተኛ ገቢ እያገኙ ሕይወታቸው መቀየሩን ተናገሩ
በደቡብ ወሎ በመኸር ወቅት የተዘራው ሰብል በሙሉ ተሰበስቧል
(c) The Ethiopian News Agency