ደሴ, የካቲት 2 ቀን 2002 (ደሴ) - በደቡብ ወሎ ዞን ከ408 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ላይ የተዘራው የመኽር ሰብል መሉ በሙሉ መሰብሰቡን የዞኑ ግብርናና ገጠር ልማት መምሪያ ገለጸ፡፡ የዞኑ ግብርናና ገጠር ልማት መምሪያ ምክትል ኃላፊ አቶ ወንዳለ ሀብታሙ ለኢዜአ.እንደገለጹት በዞኑ ወረዳዎች በመኸር ወቅት በዘር የተሸፈነው ሰብል አርሶ አደሮች እስካሁን ባደረጉት የተጠናከረ ጥረት በሙሉ ተሰብስቧል ፡፡
ሰብሉ ያለወቅቱ በሚጥለው ዝናብ ጉዳት እንዳይደርስበት ተማሪዎች ፣መምህራንና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች በዘመቻ ድጋፍ ማድረጋቸውንም አስታውቀዋል፡፡
በምርት ዘመኑ 8 ነጥብ 5 ሚሊዮን ኩንታል እንደሚገኝ ያመለከቱት ምክትል ኃላፊው፣ ይህም ከአምናው 30 በመቶ ጭማሪ እንደሚኖረው ተናግረዋል፡፡
በሌላ በኩል በዞኑ ዘንድሮ 10 ሚሊዮን ሜትር ኩብ የተፈጥሮ ማዳበሪያ ለማዘጋጀት ታቅዶ እስካሁን ግማሽ ያህሉ ተዘጋጅቶ ጥቅም
ላይ መዋሉን ገልጠዋል፡፡
የአመቱን እቅድ ተግባራዊ ለማድረግ አርሶ አደሮች ተደራጅተው እንቅስቃሴ እያደረጉ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
ሪፖ፡ያ ኤ1፡3፡00-3፡10 ጠሰድ =0.10 ጥ/መካ/
---END---