ነፃ የአየር ሰዓት ድልድልና የጋዜጣ ዓምድን የተመለከተ ዕጣ ለማውጣት ተይዞ የነበረው ፕሮግራም በፓርቲዎች ጥያቄ መሠረት ለሌላ ጊዜ ተላለፈ
አዲስ አበባ, የካቲት 1 ቀን 2002 (አዲስ አበባ) - ፓርቲዎች የምርጫ ቅሰቀሳ የሚያደርጉበት ነፃ የአየር ሰዓት ድልድልና የጋዜጣ ዓምድን የተመለከተ ዕጣ በዛሬው ዕለት ለማውጣት ተይዞ የነበረው ፕሮግራም በፓርቲዎች ጥያቄ መሠረት ለሌላ ጊዜ ተላለፈ፡፡

ፕሮግራሙ ሊተላለፍ የቻለው ፓርቲዎች ከአባሎቻችንና ከአመራሩ ጋር በተዘጋጀው የፖለቲካ ፓርቲዎች የመገናኛ ብዙሃን መመሪያ ላይ እንወያይ የሚል ጥያቄ በማንሳታቸው ነው፡፡

በዚህ መሠረት ፓርቲዎቹ ፕሮግራሙን በመጪው ረቡዕ ለማካሄድ ቀጠሮ ይዘዋል፡፡

ፕሮግራሙ የተዘጋጀው በኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣንና በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ነው፡፡

ሪ1.00ያ1.05

---END---

Headlines
ነፃ የአየር ሰዓት ድልድልና የጋዜጣ ዓምድን የተመለከተ ዕጣ ለማውጣት ተይዞ የነበረው ፕሮግራም በፓርቲዎች ጥያቄ መሠረት ለሌላ ጊዜ ተላለፈ
(c) The Ethiopian News Agency