በምስራቅ ሸዋ ከ92 በመቶ በላይ መራጮች ተመዘገቡ
አዳማ, የካቲት 1 ቀን 2002 (አዳማ) -

በምስራቅ ሸዋ ዞን በሚገኙ 11 የምርጫ ክልሎችከ92 በመቶ በላይ መራጮች መመዝገባቸዉን የዞኑ ምርጫ ቦርድ ጽህፈት ቤት ገለጠ።በዞኑ 13 የፖለቲካ ፓርቲዎች ለህዝብ ተወካዮችና ለክልል ምክር ቤት 92 እጩዎችን አስመዝገበዋል።

የዞኑ ምርጫ ቦርድ ጽህፈት ቤት አስተባባሪ አቶ ሁሴን ቲፎ ዛሬ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጡት በዞኑ ውስጥ በ11 የምርጫ ክልሎች ስር በተደራጁ 1ሺህ 051 የምርጫ ጣቢዎች 640 ሺህ 793 ሰዎች ተመዝግበው ካርድ ወስደዋል።

በዞኑ ውስጥ በአጠቃላይ ይመዘገባል ተብሎ ከሚጠበቀው 700 ሺህ ህዝብ መካከል እስከ አሁን ድረስ 92 በመቶ የሚሆነው ተመዝግቦ ካርድ መውሰዱን አስተባባሪው ገልጠዋል።

በተለይ በገላን የምርጫ ክልል የሚጠበቀው መራጭ ሙሉ በሙሉ መመዝገቡንና ከአቃቂና ዱከም የምርጫ ክልል ደግሞ 98 በመቶ መድረሱን ከአቶ ሁሴን ገለፃ ለማወቅ ተችሏል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በምስራቅ ሸዋ ዞን የሚወዳደሩ 13 የፖለቲካ ፓርቲዎች ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 35 ለክልል ምክር ቤት ደግሞ 47 እጩዎችን አስመዝግበዋል።

የፖለቲካ ፓርቲዎቹ ካቀረቧቸው እጩዎች መካከል 18ቱ ሴቶች መሆናቸውንና አምስቱ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደሚወዳደሩ የጽሀፈት ቤቱ አስተባባሪ ገልጠዋል።

ሪፖ 5፡00 2ኤዲ ከ6፡20 - - 6፡30 ጠሰድ = 00፡10 ጥጥ

---END---

Headlines
በምስራቅ ሸዋ ከ92 በመቶ በላይ መራጮች ተመዘገቡ
በደቡብ ክልል ከ85 በመቶ በላይ መራጮች ተመዘገቡ
ብአዴንና መኢብን ምርጫው ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ እንዲሆን በጋራ ለመስራት ተስማሙ
መንግሥት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ተግባራዊ እያደረገ ያለው ፖሊሲ መንግሥታዊ ባለሆኑ ባለድርሻ አካልት መታገዝ አለበት
(c) The Ethiopian News Agency