አዲስ አበባ, ሰኔ 26 ቀን 2001 (አዲስ አበባ) -የአገራችንን የፀረ-ሙስና ትግል ወደ ላቀ ምዕራፍ ያሸጋግራል ተብሎ የሚጠበቀው ብሔራዊ የፀረ-ሙስና ጥምረት ዛሬ ተመሠረተ።
ጥምረቱ የፌዴራልና የክልል መንግሥታት ፣ ሲቪል ማህበረሰብ ፣ የግሉ ሴክተርና የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎችን አካትቷል ።
የፌዴራል የሥነ ምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽነር ዓሊ ሱሌይማን የፀረ-ሙስና ትግሉን በመምራትና በማስተባበር የጥምረቱ ዓላማ እንዲሳካ መሥሪያ ቤታቸው በግንባር ቀደምትነት እንደሚሰለፍ ተናግረዋል።
ጥምረቱ መመሥረቱ አንድ ከፍተኛ ውጤት ቢሆንም የመጨረሻ ግቡ ግን መላው ኅብረተሰብ የጸረ ሙስና ትግሉ ተሣታፊ ሲሆን ፣ በሙሰኞች ላይ ጫና ፈጥሮ ሙሰኞች ሲሸማቀቁና የሙስና ወንጀል ከመፈጸም ሲታቀቡ ማየት መሆኑን ተናግረዋል ።
ብሔራዊ የጸረ ሙስና ጥምረት መሥራች አባላቱ ባወጡት የአቋም መግለጫ ጥምረቱ የፀረ-ሙስና ትግሉ በተወሰኑ ተቋማት ላይ መታጠሩ ቀርቶ መላው ሕብረተሰብ በባለቤትነትና በተዋናይነት የሚሳተፉበት እንደሆነ ተናግረዋል ።
ጥምረቱ የቆመለትን ዓላማ አሳክቷል የሚባለው በፀረ-ሙስና ትግሉ ውስጥ በቁርጠኝነት በመሳተፍና ተጨባጭ ውጤት በማስመዝገብ መሆኑም ገልጸዋል።
ሪ 11፡50 ያ 12፡15 ኤ2 1፡10 ጥአ ጠሰድ 1፡20
---END---