አዲስ አበባ, ሰኔ 26 ቀን 2001 (አዲስ አበባ) - ፕሬዝዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ በአዲስ አበባ ነፃ የሕክምና አገልግሎት ለመስጠት የመጡትን የሳዑዲ ዓረቢያ የሕክምና ቡድን አባላት በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ፡፡ከኘሬዝዳንት ግርማ ጋር ከተነጋገሩት የቡድኑ አባላት መካከል ፕሮፌሰር ማዝን አልህጅራ እንደገለጹት ከተለያዩ የህክምና ዘርፎች የተውጣጡት የቡድኑ አባላት ከሚሰጡት ነጻ ህክምና በተጨማሪ በከተማዋ ያሉ ዩኑቨርስቲዎችና ሆስፒታሎች የሚያስፈልጓቸውን በማየት ወደ አገራቸው ሲመለሱ ሪፖርት ያደርጋሉ፡፡
ዩኒቨርስቲዎችና ሆስፒታሎች የሚያስፈልጓቸውን የስራ መሣሪያዎች እንዲያገኙና የሌሉ የህክምና አገልግሎቶችም እንዲኖሩ ለማድረግ ጥረት እንደሚያደርጉ ተናግረዋል፡፡
በከተማዋ ያለው አጠቃላይ የጤና ሁኔታ ጥሩ እንደሆነና በከተማዋ የጤና አጠባበቅ ስርዓትም መደሰታቸውን የህጻናት ህክምና ስፔሻሊስት የሆኑት ዶክተር አብደላ አልመጥረፊ ተናግረዋል፡፡
በከተማዋ የመጀመሪያ ደረጃ የህክምና አገልግሎትና የጤና ትምህርት እንደሚያስፈልግ የገለጹት ዶክተር አብደላ የጤና ሁኔታው በአጠቃላይ ግን ጥሩ የሚባል መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ስ-9፡00 መ-10፡41 ሪ-10፡48 ያ-11፡09
---END---