የፌዴሬሽኑ መመስረት ወጣቶች አዲሲቱን ኢትዮጵያን የመገንባት ሚናቸውን እንዲወጡ የሚያስችል ነው-ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ
አዲስ አበባ, ሰኔ 26 ቀን 2001 (አዲስ አበባ) - የኢትዮጵያ ወጣቶች ፌዴሬሽን መመስረት ወጣቶች አዲሲቱን ኢትዮጵያን ለመገንባት ያላቸውን መተኪያ የለሽ ሚና በብቃት እንዲወጡ የሚያስችላቸው መሆኑን ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ ገለጹ፡፡ የኢትዮጵያ ወጣቶች ፌዴሬሽን ምስረታ ጉባኤ ዛሬ ተጀምሯል፡፡

ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ በምስረታ ጉባኤው ላይ እንደተናገሩት መንግሥት በአደረጃጀትና በአሰራር ረገድ ለወጣቶች ብቃት፣ ተሳትፎና ተጠቃሚነት መረጋገጥ ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል፡፡

ለአብነትም የወጣቶች የስፖርት ሴክተር መዋቅር መደራጀቱን፣ የወጣቶች ብሔራዊ ፖሊሲ መውጣቱን እና የወጣቶች የዕድገት ፖሊሲ ተቀርጾ በወጣቶች ሙሉ ተሳትፎ በመተግበር ላይ መሆኑን ፕሬዚዳንት ግርማ ተናግረዋል፡፡

የወጣቶች እና ስፖርት ሚኒስትር ወይዘሮ አስቴር ማሞ በበኩላቸው ወጣቶቹ ፌዴሬሽን መመስረታቸው ከዚህ በፊት ባቋቋሟቸው በርካታ ማህበራት በተናጥል ያደርጉት የነበረውን ትግል በአንድ ላይ በመሆን የጋራ ጥቅማቸውን ያስጠብቅላቸዋል ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ወጣቶች የአገራቸው የፖለቲካ ስርዓት በፈጠረላቸው በነፃ የመደራጀት መብት በመጠቀም የወጣቶች ፌዴሬሽን ማቋቋማቸው በኢኮኖሚ፣ በፖለቲካ እና በማህበራዊ ዘርፍ ጥቅሞቻቸውን እንዲያስጠብቁ የሚያስችላቸው መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ወጣቶች ፌዴሬሽን ምስረታ አስተባባሪ ኮሚቴ ሊቀመንበር ወጣት ውብሸት ገብረ እግዚአብሔር በበኩሉ ባለፉት አምስት ወራት ኮሚቴው በርካታ ተግባራትን ማከናወኑን አስረድቷል፡፡

ለአብነትም ሁለት ጊዜ በሁሉም ክልሎችና በሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች በሚገኙ ዞኖች፣ ክፍለ ከተሞችና ወረዳዎች መላውን ወጣት ያሳተፈ የወጣቶች የተሳትፎና የንቅናቄ ኮንፍረንስ ማካሄዱን ተናግሯል፡፡

በውይይቱ ላይም ከስምንት ሚሊዮን የሚበልጡ ወጣተች ተካፋይ መሆናቸውን ተናግሯል፡፡

በምስረታው ጉባኤ ላይ የፓን አፍሪካ ዩዝ ካውንስል የላከው መልዕክት የተነበበ ሲሆን የምስረታ ጉባኤው በነገው ዕለትም እንደሚቀጥል የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዘግቧል፡፡

ሪ6፡00 ያ6፡47 ኤ9፡34 ጠሰድ3፡34 ተ9፡34

---END---

Headlines
የፌዴሬሽኑ መመስረት ወጣቶች አዲሲቱን ኢትዮጵያን የመገንባት ሚናቸውን እንዲወጡ የሚያስችል ነው-ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ
የህንድና የኢትዮጵያ ግንኙነት ከወዳጅነት ወደላቀ የኢኮኖሚ ትብብር መስክ ማደግ ችሏል-አምባሳደር ጉርጂት ሲንግ
በግልገል ጊቤ ሶስት የታችኛው ተፋሰስ አካባቢ ነዋሪዎችን አኗኗር መለወጥ የሚያስችሉ ፕሮጀክቶች መቀረጻቸውን ኮርፖሬሽኑ አስታወቀ
በኃይል ቆጣቢ አምፑሎች 82 ሜጋዋት ማዳን ይቻላል - ኮርፖሬሽኑ
(c) The Ethiopian News Agency